tg-me.com/nibab_lehiwot/153
Last Update:
ከታዘብኩት.......
እያንዳንዳችን ለምን ብለን ብዙ ጠይቀን መልስ ያጣንላቸው ጥያቄወች በውስጣችን አሉ። ማጥፋት ፈልገን የማይጠፉ፣ ማመን ፈልገን የሚያጠራጥሩን፣ መርሳት ፈልገን የማይረሱን፣ ብቻ ብዙ ብዙ ነገር ውስጣችን አለ። (የዛሬ ጥያቄዬ ለምን ብቻውን የሚያወራ ሰው እብድ እየተባለ ይጠራል?)
አንዱ ነውኮ...... ዛሬ ብቻውን እያወራ እየሔደ ይሄ ሰውዬ እብድ ነው ብሎ ጭንቅላቴ ደመደመ። በመጀመሪያ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ከንፈሬን መጠጥ አድርጌ ኑሮ ያሳበደው ምስጊን ሕዝብ አልኩ (በውስጤ) ይሔንን ስል ግን አንዱ የአእምሮየ ክፍል(ምን እንደሚባል እኔ እንጃ) ድንገት ከተኛበት በቀዝቃዛ ውሃ እንደተዘፈቀ ሰው ብንን ብሎ ነቃ........
እሱ:- ለምን እብድ መሰለሽ?
እኔ:-ብቻውን እያወራ ነዋ.....
እሱ:- ብቻ ማውራት እንደ እብድ እንደሚያስቆጥር እንዴት አወቅሽ.......
እሱ:- ቀላል ጥያቄ ከልጅነቴ ጀምሮ እያየሁት እና እየተነገረኝ ያደግኩት ብቻውን የሚያወራ ሰው ጤነኛ እንዳልሆነ ነው።
እሱ:-እና ስለተነገረሽ ብቻ አምነሽ ተቀበልሽ አትጠራጠሪም?
እኔ:- ለምን እጠራጠራለሁ?
እሱ:- ለምን አትጠራጠሪም?..........
(በጣም ብዙ ብዙ... የለምን? ክርክር)
እሱ:- ማስረጃ አቅርቢ.....
እኔ:- አንተ ማስረጃ አቅርብ.....
እሱ:- እብድ ነሽ እንዴ?
እኔ :- አይደለሁም
እሱ:- ነሽ
እኔ :- ለምን እንደዛ አልክ?
እሱ:- ብቻሽን እያወራሽ ነዋ
እኔ:- እንዴ መቼ?
እሱ :- አሁን !!!
እኔ:- ከአንተ ጋ አይደል እንዴ እያወራሁ ያለሁት
እሱ:- ማን ነኝ እኔ እስኪ ዞር ዞር በይ እኔ የለሁምኮ
አንዴ ወደ ግራ አንዴ ወደ ቀኝ ዞር ዞር አልኩ ማንም የለም። አማተብኩ ከማን ጋ ነበር እያወራሁ የነበረው?
እሱ:- አየሽ እብድ ነሽ ያው ማስረጃ ብቻሽን እያወራሽ ነው........
እኔ:- ዝም በል......ሳላስበው ዛፍ ላይ የነበሩት ወፎች በድንጋጤ እስኪበሩ ድረስ ጮህኩ።
በረጅሙ ተነፈስኩ እና አካባቢየን ቃኘት አደረግኩት። ለራሴ የተሰማኝ ከሆነ ቦታ ቆይቼ አሁን ወዳለሁበት ቦታ እንደተመለስኩ ነው።
ወይኔ ጉዴ ሰው ሁሉ ወደ እኔ እያፈጠጠ ነው።
አበድኩ እንዴ?🤔
@nibab_lehiwot
@nibab_lehiwot
@nibab_lehiwot
BY ሕይወትን - በገፅ
Warning: Undefined variable $i in /var/www/tg-me/post.php on line 283
Share with your friend now:
tg-me.com/nibab_lehiwot/153